ይህ የስዊድን ትምህርት ቤት ነዉ

ልጅዎ 1 ዓመት ከመሙላቱ ቀን ጅምሮ ወደ ቅድመ ትምህርት (መዋዕለ ህፃናት) መሄድ ይችላል። ቅድመ ትምሀርት ቤት በፈቃደኝነት ነዉ። ልጅዎ ሠስት ዓመት ከሞላዉ ዓመት መኸር ጀምሮ ልጁ ወደ አጠቃላይ የመዋዕለ ህጻናት ትምሀርት ቤት የመጀመር መብት ኣለዉ። አጠቃላይ መዋዕለ ህጻናት 15 ሰዓት በሳምንት ሆኖ ከክፍያም ነጻ ነዉ።

ተማሪዉ 6 ዓመት ዕደሜ ከሞላ ጀምሮ፡ በቅድመ-ትምህርት ቤት (ጀማሪ ክፍል) ይጀምራል። ከቅድመ-ትምህርት ቤት ክፍል በኋላ ልጆቹ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ወይም ተመጣጣኝ የትምህርት ቤት ቅጾችን ይጀምራሉ። ከ 6 እስከ 13 ዓመት ዕድሜ ለሆኑ ተማሪዎች፡ ከትምህርት ሰዓት በፊት እና በኋላ እንዲሁም በበዓላት ወቕት ክፍት የሆኑ እና ትርጉም ያለዉ እንቅስቃሴዎችን የሚያደርጉ የነጻ ጊዜ ማሳለፍያ ማዕከሎች ኣሉ። ክፍያዉ በአሳዳጊ ወይም ወላጂች ገቢ ላይ የተመሠረተ ነዉ።

በስዊድን ዉስጥ የትምሀርት ግዴታ ኣለን፣ ይህም ማለት ተማሪዉ ከመዋዕለ ሕፃናት እስከ 9 ኛ ክፍል መማር ያለበት ሕግ ነዉ። ተማሪዉ ከታመመ፡ ተማሪዉ በቤት ዉስጥ የሚቆያቸዉ እያንዳንዱ ቀን ለትምሀርት ቤቱ ማሳወቅ ኣለብዎት። የሕመም እረፍት ሪፖርት ማድረግ የሚችለዉ የተማሪዉ ሞግዚት (ወላጅ) ብቻ ነዉ።

የስዊድን የትምህርት ቤት ባህል፡ ከየቀድሞ የትምህርት ቤት ልምዶችዎ ሊለይ ይችላል። ስለ ሆነም፡ በርስዎ ተማሪዎች እና ኣሳዳጊዎች ላይ ሌላ ግዴታዎች እና መስፈርቶች ሊያጋጥሙ ይችላሉ።

እኛ ከተማሪዉን የምንጠብቃቸዉ ነገሮች:

  • በሰኣቱ መድረስ።
  • የቤት ሥራዎችን በወቅቱ ማቅረብ።
  • በየትምህርት ቤት ንብረት፡ መምህራን እና የትምህርት ቤት ጓደኞቻችዎ ኣክብሮት ማሳየት።
  • በየትምህርት ቤት በንቃት መሳተፍ። መልስ ለማግኘት እንዴት እንዳሰቡ መግለፅ መቻል፡ ቢያንስ ትክክለኛ መልስ ከማግኘት ጋር በጣም ኣስፈላጊ ነዉ።
  • በቡድን መሥታት እና ዳሰሳ ጥናቶች፣ ዉይይቶች ላይ በንቃት መሳተፍ። አንድ ግብ ላይ ለመድረስ ኣብሮ መሥራት።
  • በተግባራዊ ዓይነት ትምህርቶች መሳተፍ፡ ለምሳሌ፡ በየቤት ሥራ፣ ስእል (ምስል) እና በሙዚቃ ዓይነት ትምህርቶች። እነዚህ ዓይነት ትምህርቶች እንደ ሌሎች ንድፈ ሃሳባዊ ትምህርቶች ኣስፈላጊ ናቸዉ።

ኣሳዳጊዎች ከትምሀርት ቤቱ ጋር መገናኘት እንዲኖራቸዉ ይጠበቃል። በትምህርት ቡቱ እና በወላጆች መካከል ጥሩ ትብብር ቢኖር ለሁለቱም ወገኖች ይጠቅማል። ስለኖነም ስለ ትልቅ እና ትንሽ ለሚመለከቱ ነገሮች ከእኛ ጋር በመገናኘት ይወያዩ።

የመሠረታዊ እሴቶች አሠራር

የትምህርት ቤቱ እሴቶች እና ተልእኮ በዲሞግራሲ መሠረት እና እንዲሁም በመምህራን አመራር ላይ የተመሠረተ ነዉ።

ትምህርቱ፡ የሰብኣዊ መብቶችን እና የስዊድን ህብረተሰብ የሚያርፍባቸዉን መሰረታዊ የዴሞክራሲ እሴቶች ኣክብሮት ማስተላለፍ እና መልህቅን መልቀቅ አለበት።

የሁሉም ሰዎች እኩል እሴት፣ የሴቶች እና የወንዶች እኩከልነት እና በሰዎች መካከል ያለዉ ኣንድነት፡ ትምህት ቤቱ መቅረፅ እና ማስተላለፍ ያለበት እሴቶች ናቸዉ። በትምህርት ቤቶች ዉስጥ ማስተማር፡ ሃይማኖታዊ ያልሆነ መሆን ኣለበት።

ትምህርት ቤቱ፡ በተባበሩት መንግስታት የሕፃናት መብቶች ስምምነት (የሕፃናት መብቶች ስምምነት) ዉስኢጥ የተገለጹትን እኤቶች እና መብቶች መቅረጽ እና ማስተላለፍ ኣለበት።

በቬርምዶ ማዘጋጃ ዉስ ያሉ ትምህርት ቤቶችን በተመለከተ መረጃ

የቬርምዶ ማዘጋጃ ትምህርት ቤቶች

በየቬርምዶ ማዘጋጃ፡ ኣስር የማዘጋጃ ቤቱ ትምህርት ቤቶች እና ኣራት የግል መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አሉ።

በሄምስታ ትምህርት ቤት እና በቬርምዶ ሴርጎርድ ትምህርት ቤት ዉስ ተማሪዎች የትምህርት ቀንን በከፊል ወደ ኣንድ ትንሽ የማስተማሪያ ቡድን የሚሄዱባቸዉ የዝግጅት ክፍሎች አሉ። በቀሪዉ ጊዜ ተማሪዉ ወደ ትልቁ ክፍል ይሄዳል።

አስተባባሪ

ሁሉም ኣዲስ የመጡ ተማሪዎች እና አሳዳጊዎች፡ አስቀድመዉ የተማሪዉ ቋንቋ እና በትምህርት ቤት ተመኩሮ ላይ ደረጃዉን ለማወቅ በሚደረግ የዳሰሳ ጥናት ላይ ለመሳተፍ ከአንድ የማዘጋጃ ቤቱ አስተባባሪዎች ጋር ይገናኛሉ። የዳሰሳ ጥናቱ ዉጤት፡ ለትምህርት ቤቱ ለተማሪዉን ጥሩ ምደባ የማድረግ እድል የሚሰጥ ከመሆኑም በላይ፡ አስተማሪዉ ትምህርቱን ከተማሪዉ የእዉቀት እና ፍላጎት ደረጃ ጋር ለማጣጣም እድል ይሰጠዋል።

አማካሪ / የክፍል ኣስተማሪ

አማካሪዉ / የክፍል ኣስተማሪዉ፡ ለተማሪዉ በትምህርት ቤቱ እና በቤት መካከል ኣስፈላጊ ኣገናኝ ነዉ። är አማካሪዉ / የክፍል ኣስተማሪዉ የተማሪዉን የእዉቀት እድገት እና የተማሪዉን ማህበራዊ እድገት ይቆጣጠራል። ልዩ ፍላጎቶች ካሉ ወይም ከተነሱ፡ እርምጃዎች የመዉሰድ ሃላፊነት ያለዉ ኣማካሪዉ / የክፍል ኣስታመሪዉ ነዉ።

መሰናዶ ወይም የዝግጅት ክፍል እና ስዊድንኛ እንደ ሁለተኛ ቋንቋ

የዝግጅት ክፍል

ወደ መሰናዶ ክፍል የሚሄድ ተማሪ፡ ተማሪዉ ከሚሄድበት ደንበኛ ክፍል ዉጭ፡ በትንሽ የማስተማሪያ ቡድን ዉጭ በሌላ ክፍል ከፊል ትምህርትን ይሄዳል። የመሰናዶ ከፍል ዓላማ፡

ተማሪዉ በትልቅ ክፍል ዉስጥ ትምህርትን ለመከታተል በቂ እዉቀት ማግኘት እንዲችል፡ በስዊድንኛን በቂ እዉቀት መዳበር ስላለበት ነዉ። አንድ ተማሪ ቢበዛ ለ 2 ዓመታት ያህል በመሰናዶ ክፍል ይማራል።

ስዊድንኛ እንደ ሁለተኛ ቋንቋ

ተማሪዎችን በትልቅ ክፍል ዉስጥ ማስተማርን ለመምሰል የሚያስችል በቂ የቋንቋ ችሎታ ያለቸዉ ተማሪዎች የስዊድን ቋንቋን ለማጥለቅ እና ለማዳበር፡ በስዊድንኛ እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ይሰጣሉ። ለሁለተኛ ቋንቋ የስዊድን የትምህርት መርሃግብር ከስዊድንኛ ትምሀርት እኩል ነዉ፡ ነገር ግን ተማሪዉ ሌላዉን የአፍ መፍቻ ቋንቋ በተመለከተ ይገመገማል።

በቤት እና በትምህርት ቤት መካከል የሚደረግ ግንኙነት እና መግባባት

በማዘጋጃ ቤቱ ዉስጥ ያሉ ትምህርት ቤቶች ከተማሪ እና ከአሳዳጊዎች ጋር በድር-ተኮር መሣርያ አመካኝነት የትምህርት ቤት መድረክ፡ ስኩልሶፍት ተብሎ በሚጠራዉ መንገድ ይገናኛሉ። እዚያ፡ ተማሪዉ ከታመመ ሪፖርት ያደርጋሉ፡ ከኣማካሪ / የክፍል ኣስተማሪን በዛ ያነጋግሩ እና የልጅዎን የእዉቀት እድገት በግምገማዎች፡ ምዘናዎች እና ደረጃዎች ይከታተላሉ።

እርስዎ ስለ የልጅዎ የትምህርት እድገት ከኣመካሪ / የክፍል አስተማሪ ለመነጋገር የያዝዎት ቆጠሮም በስኩልሶፍት ይለጠፋል። በእነዚህ ዉይይቶች ወቅትተ፡ ነገሮች በትምህርት ቤት ዉስጥ እንዴት እንደሚሄዱ፡ በተለያዩ የትምህርት ዓይነቶች ዉስጥም የተማሪዉ እድገት ይወያዩ እና ጥያቄዎች ሲኖርዎትም የመጠየቅ ዕድል ያገኛሉ።

በስኩልሶፍት መንገድም፡ ስለ የወላጅ ስብሰባዎች መረጃም ያገኛሉ። እነዚህ ስብሰባዎች ከትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህራን እሰከ ሞግዚቶች ድረስ ያሉ በመሰብሰብ አጠቃላይ መረጃዎች የሚገኙበት ስብሰባዎች ናቸዉ።

የመግብያ ዝርዝር ከየትምህት ቤቱ ረሲፕሽን ያገኛሉ

ከትምህርት በኋላ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች

ከትምህርት ቤት በኋላ የሚከናወኑ ትግባራት ወይም እንቅስቃሴዎች፡ ለቋንቋ እድገት፡ ለማህበራዊ ግንኙነቶች እና ዉህደትም አስተዋፆዖ ያደርጋሉ። ስለዚህ ከትምህርት ቤት በኋላ ከትምህርት ቤት ጓደኞች ጋር በትምሀርት ቤት መቆየቱ አዎንታዊ ሊሆን ይችላል። በቅድመ-ትምህርት ቤት እስከ 3 ኛ ክፍል ላሉት ታዳጊ ተማሪዎች መዝናኛ የሚሰጥ ሲሆን፡ በ 4ኛ፡ 5 ኛ እና 6 ኛ ክፍል ላሉት ትልልቅ ተማሪዎችም ክሉበን (ክበብ) ተብሎ የሚጠራዉ ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ይደረጋል።

በትላልቅ ዕድሜዎች ላይ ላሉ ተማሪዎች፡ እንደ እግር ጓስ ስልጠና ባሉ ስፖደርት ዉስ መሳተፍ ጥሩ ሊሆን ይችላል። የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እነዲሁ ጤናን የሚያበረታታ ሲሆን፡ ሌሎች በርካታ ጥቅሞችም አሉት። ቶምተቡ (Tomtebo) በሄምስታ ትምህርት ቤት ስፖረድት ኣደራሽ ላይ ይገኛል እና የተለያዩ እንቅስቃሴዎችም ኣሉት። ሆኖም፡ ይህ ትምህርት ቤቱ የሚያዘጋጀዉ እንቅስቃሴ ኣይደለም።

ዕረፍቶች

በእረፍት ጊዜ ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ነፃ ናቸዉ። በሌሎች ጊዜያት ዕረፍት ከፈለጉ፡ ለአማካሪ ወይም አርእሰ መምህሩ ማመልከት ኣለብዎት። ማመልከቻዉ በጽሑፍ ለየክፍል ኣስተማሪ ወይም አመካሪ መቅረብ ኣለበት።

በትምህርት ቤት ዕረፍቶች ወቅት፡ የመዝናኛ ጊዜ ለታዳጊዎች ክፍት ነዉ። ሆኖም ግን እርስዎ እንደ ሞግዚት ለዚህ ኣስቀድመዉ ማመልከት ያስፈልግዎታል።

የተማሪ ጤና ቡድን

በቬርምዶ ማዘጋጃ ቤት ዉስጥ ባሉት በእያንዳንዱ የማዘጋጃ ትምህርት ቤቶች፡ ነርስ፣ ኣማካሪ፣ ልዩ ኣስተማሪ፣ ልዩ መምህር፣ የጥናትና ሙያ አማካሪ እና ምክትል ርዕሰ መምህራን ያካተተ የተማሪ የጤና ቡድን ኣለ። የትምህርት ቤት ዶክቶሮች እና የትምህርት ቤት የስነ ልቦነ ባለ ሞያ (ሳይኮሎጂስት) በሥራ ላይ ይገኛሉ፡ ነገር ግን በአንድ የተወሰነ ትምህርት ቤት ዉስ አይቀመጡም።

የቡድኑ ተግባር፡ የተማሪዎችን እድገት እና ትምህርት በተመለከተ የመምህራንን የትምህርት አሰጣጥ ብቃት ማሟላት ነዉ። ቡዱኑ ከመምህራን እና ከሌሎች የትምህርትተ ቤት ሰራተኞች ጋር በተቻለ መጠን ለተማሪዎች ጥሩ የመማር ሁኔታ አስተወፅኦ ለማድረግ ይሠራል።

ቅጾች ለመሙላት እና ለማስገባት

ኣስቸኳይ (SOS) ቅጾች - ስለ የተማሪ እና የአሳዳጊዉ ኣድራሻ እና ስልክ ቁጥር መረጃ የያዘ ቅጽ። ይህ ደግሞ፡ የመድኃኒነት፡ የመዋኛ ችሎታ፡ ፎቶግራፍ መንሳትን በተመለከተ ለሚነዉ ያቄዎች መልስ ይሰጣል።

ልዩ ኣመጋገብ - ተማሪዉ በአለርጂ ወይም በሃይማኖታዊ ምክንያቶች ልዩ የምግብ ፍላቶት ካለዉ። ቅጹ ለኣማካሪ ነዉ የሚሰጠዉ።

ነጻ ግዜ ማሳለፍያ / ክበብ (ክሉበን) - የመዋለ ሕፃናት ክፍል እና ከ1 – 6 ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በመዝናኛ ማእከል እና በክለብ እንቅስቃሴዎች ዉስ ቦታ ማመልከት ይችላሉ። ቅጹ ለኣማካሪ ነዉ የሚሰጠዉ።

ሞምፑዩተር - ከ 4ኛ ክፍል ጀምሮ ተማሪዎች ኮምፒርን እንደ መማሪያ መሳሪያ መበደር ይችላሉ። ኣሳዳጊ እና ተማሪ፡ በብድር ጊዜ ዉስ የሚሠሩትን ህጎች አብሮ በማንበብ ዉሉን መፈረም አለባቸዉ። የብድሩ ኃላፊነት የኣሳዳጊዎች ነዉ። ቅጹ ለአማካሪ ነዉ መሰጠት ያለበት።

የአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት - በበርካታ ቋንቋዎች የቀረበ እና በጧም የሚመከር ትምህርት ነዉ። የተደረጉት ጥናቶች እንደሚያሳየዉ በአፍ መፍቻ ቋንቋ ማስተማር፡ ተማሪዉ በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ዉስጥ በእዉቀት እድገት ላይ ግልጽና አዎንታዊ ዉጤት አለዉ።

ትምህርቱ የሚመራዉ በትምህርቱ እቅዶች እና በርዕሰ-ጉዳዩ ዕቅዶች ነዉ። ስለሆነም ተማሪዉ በርዕሱ ዉስጥ ዉጤቶችን ማግኘት ይችላል።

ማመልከቻዉ፡

ወደ ፋርስታቪክ ትምህርት ቤት / የአፍ ማዉጫ ትምህርት (Farstavikens skola/modersmål Bergsgatan 13441 Gustavsberg) ነዉ የሚላከዉ።

የአዉቶቡስ ካርድ - ኣሳዳጊዎች ራሳቸዉ ናቸዉ የኣዉቶቡስ ካርድ ከቬርምዶ ማዘጋጃ ቤት የሚያመለክቱ። ከትምህርት ቤቱ በ4 ኪ.ሜ. ርቀት ዉስጥ የሚኖሩ ተማሪዎች፡ በአብዛኛዎቹ አጋጣሚዎች የአዉቶቡስ ካርድ አይሰጣቸዉም። የአዉቶቡስ ካርድ ለማግኘት ከተፈቀደላቹ፡ ከየትምህርት ቤቱ ቢሮ ነዉ የምትወስዱት።